top of page

ነሐሴ 25፣2016 - ግብፅ በሶማሊያ ወታደሮቿን ብታሰፍር፤ ለኢትዮጵያ ስጋት የሚሆነው ለምንድነው?

  • sheger1021fm
  • Aug 31, 2024
  • 1 min read


የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሊተነበይ ወደማይችል ፈተና ውስጥ እየገባ ነው ይላል በዚህ ሳምንት የወጣው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፡፡


ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሰነድ ከፈረሙበት ያለፈው ጥር ጀምሮ በሶማሊያ መንግስት በኩል የተቆሰቆሰው ቁጣ ሌሎችም እንጋራዋለን እያሉ ውጥረቱን አንረውታል፡፡


ግብፅ ሶማሊያን የነካ ጠላቴ ነው ማለት ብቻ ሳይሆን ወታደሮቿን ወደሞዲሾ እየላከች ነው፡፡


የሰላም አስከባሪነቱንም እኔ እገባበታለሁ ብላ ለአፍሪካ ህብረት ማመልከቻ አስገብታለች፡፡


በህዳሴ ግድብ ምክንያት ከግብፅ ጋር ዓይንና ናጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ፈተና ብላ የጠራችው ስጋት “ያሰጋኛል” ብላለች፡፡


ለመሆኑ ስጋቷ ምንድነው? ለምንስ ትሰጋለች?


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page