የጅቡቲ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማህሙድ አሊ የሱፍ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው ይህንን የተናገሩት፡፡
ጅቡቲ ሀሳቡን እንደአማራጭ ያቀረበችው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የገቡበትን ውጥረት ለማርገብ ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ እራሷን ነፃ ሀገር ነኝ ከምትለው እና ሶማሊያ ደግሞ የግዛቷ አካል አድርጋ ከምትቆጥራት ሶማሌላንድ ጋር በወደብ ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት መፈረሟ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎም በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል ውጥረት ተፈጥሯል፡፡
ይሄንኑ ውጥረት ለማርገብ አማራጭ ሀሳብ ያቀረበችው ጅቡቲ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል የታጁራ ወደብ ከኢትዮጵያ ድንበር በጣም ቅርብ በመሆኑ መቶ በመቶ እንድታስተዳድረው እንፈቅድላታለን ማለቷ ተሰምቷል፡፡
የጅቡቲ መንግስት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ችግራቸውን በመነጋገር እንዲፈቱ ይፈልጋል ያሉት የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ አልሸባብ በአካባቢው አሁንም ስጋትቱ አልቀነሰም ብለዋል፡፡
ይህ ደግሞ በአካባቢው ያለውን ፀጥታ እንዳያደረፈርስ ስጋት አለን ሲሊ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
ጅቡቲ ስላቀረበችው አማራጭ ሀሳብ በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
በረከት አካሉ
Commenti