top of page

ነሐሴ 25፣2016 - ከ6 ዓመታት በኋላ የልደት ምዝገባን 100 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 31, 2024
  • 1 min read

ከ6 ዓመታት በኋላ(እ.ኤ.አ 2030) የልደት ምዝገባን 100 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡


ይህ የተነገረው ዛሬ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው 7ኛው የሲቪል ምዝገባና ቫይታል እስታቲስቲክስ እየተከበረ ባለበት መድረክ ላይ ነው ፡፡


የኢሜግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በ2030 #የልደት_ምዝገባን መቶ በመቶ እንዲሁም የሞት ምዝገባን ደግሞ 80 በመቶ ለማድረስ አቅደን እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


የሲቪል ምዝገባ እና ባይታል ስታትስቲክስ መረጃ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟንና ደህንቷን ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ዳይሬክተሯ አስረድተዋል፡፡

የሲቪል ምዝባና ቫይታል ስታትስቲክስ ምዝገባ የሚካሄደውን የልማት እና የዲሞክራሲ ሥርዓት ለማሳካት መልካም አስተዳደር ለማስፈን የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ሰላማዊት ዳዊት አስረድተዋል፡፡


የሲቪል ምዝገባና ቫይታል እስታቲስቲክ ምዝገባ በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀፅ 6 ላይ ‘ማንኛውም ሰው በህግ ፊት መታወቅ አለበት’ የሚለውን ለማሳካትም ይረዳል ብለዋል፡፡


በፈረንጆቹ 2030 ሁሉም ሰው የልደት ምዝገባን ጨምሮ ህጋዊ የማንነት ማስረጃ ሊኖረው እንደሚገባ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ጠቅሰዋል፡፡


‘’የሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታትስቲክስ በቴክኖሎጂ በማዘመን ከህጋዊ መታወቂያ ሥርዓቶች ጋር በማገናኘት ግለሰቦች በይፋ እውቅናና የማንነት ሰነድ እንዲኖራቸው በመብቶቻቸው እንዲጠቀሙ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥም እንዲሳተፉ ያስችላችዋል’’ ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ የስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ‘’የሲቪል ምዝገባና ቫይታል መረጃ የሚፈለገውን ያህል ስላልተሰራበት ዜጎች በኢኮኖሚው፣ በጤናው እና በፍትህ ሥርዓት ውስጥ እንዳይጠቀሙ እያደረጋቸው ነው’’ ብለዋል፡፡


ችግሩን ይህንን ለመፍታትም እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page