በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ደንብ ተላልፈው የተገኙ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ66 ሚሊዮን ብር በላይ የቅጣት ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናገረ፡፡
ባለስልጣኑ ባለፈው አንድ ወር ብቻ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በህግ ጥሰት እርምጃም ወደ 25 ሚሊዮን ብር ሰብስቤአለሁ ብሏል፡፡
ከደንብ ተላላፊዎች የተገኘው ገንዘብም ለፋይናንስ አስተዳደር ገቢ ሆኖ መልሶ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠሩንም ባለስልጣኑ ተናግሯል፡፡
ህገወጥ ንግድን ከመቆጣጠር እና የተለያዩ የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከል አኳያ ትልቅ መሻሻሎች መጥተዋል ተብሏል፡፡
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባከናወነው ስራም የመሰረተ ልማቶች ውድመት እና ብልሽት እየቀሰነ መምጣቱም ተጠቅሷል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
Kommentare