በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በአብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኞላ በተባለ ቦታ በደረሰው የመሬት መንሸራተት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች እስካሁን ምንም ዓይነት የአስቸኳይ የእለት ድጋፍ አላገኙም ተባለ።
በመሬት መንሸራተት ሳቢያ የተፈናቀሉ የቤተሰብ አባላት ቁጥር 2,400 መሆናቸውንም ሰምተናል።
የጠለምት ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ወርቅነህ ‘’በወረዳው በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የአካባቢውን ነዋሪዎች ወደ ሌላ ቀዬ እንዲሰፍሩ ቢደረግም አደጋው ከተከሰተበት ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ምንም ዓይነት ድጋፍ አላገኙም’’ ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ አያይዘውም በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ፣የመንገድ ፣ የኔትወርክ ፣ የባንክ እና መሰል የመሰረተ ልማት ችግር በመንግስት በኩልም ሆነ ከተለያዩ እረጅ ድርጅቶች ድጋፍ ለማግኘት መቸገራቸውን ለሸገር ተናግረዋል።
ፍቅሩ አምባቸው
Comments