ነሐሴ 24፣2016 - በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የመንግስት መ/ቤቶች ንብረት ያላግባብ በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ ኦዲት አረጋገጠ
- sheger1021fm
- Aug 30, 2024
- 1 min read
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የመንግስት መ/ቤቶች ንብረት ያላግባብ በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ ኦዲት አረጋገጠ፡፡
የኦዲት ምርመራው 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ አሳይቷል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 269 ተቋማት ላይ በተደረገ የንብረት ቆጠራ ወደ 24 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በጉድለት መገኘትንም ሰምተናል።
ጉድለት የተገኘባቸው የተቋማት ሃላፊዎች ላይም እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ #የመንግስት_ንብረት_አስተዳደር_ባለስልጣን የህንፃና ንብረት ኦዲት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ምሩጽ ታዬ፤ በተቋማቶች ላይ ከተገኘው ጉድለት ውስጥ ወደ 10.9 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል።
አቶ ምሩፅ አያይዘውም በተቋማቱ ከተመዘገበው ንብረት ላይ ጉድለት የተገኘባቸው ሃላፊዎች ከስራ ገበታ እንዲባረሩ እና በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ሲሉ ነግረውናል።
ፍቅሩ አምባቸው
Comments