ነሐሴ 23፣2016 - የኢትዮጵያ አንድ ኪሎ ቡና በ102,000 ብር በላይ ተሸጠ
- sheger1021fm
- Aug 29, 2024
- 1 min read
የኢትዮጵያ አንድ ኪሎ ቡና በ102,000 ብር በላይ ተሸጠ።
ይህም በታሪክ ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።
በአራተኛው የባለልዩ ጣዕም ቡና ውድድር (ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) ዓለም አቀፍ ጨረታ የኢትዮጵያ አንድ ኪሎ ቡና በ980 ዶላር ወይም ከ102,000 ብር በላይ መሸጡን እና አዲስ ክብረ ወሰን መመዘገቡን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ በቡና ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች የልፋታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ውድድር ከተጀመረ አምስት ዓመት ማስቆጠሩን ጠቅሰዋል።
አራተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር በተለያዩ የውድድር መርሃ ግብሮች ላለፉት ሰባት ወራት ሲካሄድ መቆየቱን ተነግሯል።
በዘንድሮው የውድድሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ጨረታ ሂደት ተወዳዳሪ ለሆኑት ቡናዎች 4,870 የተለያዩ ዋጋ መሰጠቱንና ለአንድ ኪሎ ቡና የቀረበው የጨረታ ዋጋ ታሪካዊ ሆኖ መመዝገቡን ጠቁመዋል።
ውድድሩን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ ተቋማት፣ አርሶ አደሮች፣ በቡናው ዘርፍ የተሰማሩና አጋሮች ዳይሬክተሩ ምስጋና አቅርበዋል።
አምስተኛው የባለልዩ ጣዕም ቡና ውድድር(ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) በ2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።
ንጋቱ ሙሉ
Commentaires