ነሐሴ 23፣2016 - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን አጀንዳ በሰበሰብኩባቸው ክልሎች ያልተሳተፉ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም አለ
- sheger1021fm
- Aug 29, 2024
- 1 min read
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን አጀንዳ በሰበሰብኩባቸው ክልሎች ያልተሳተፉ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም አለ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ላይ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሆነው የሚንቀሳቀሱ #የፖለቲካ_ፓርቲዎች በአጀንዳ አሰባሰብ ሒደት ላይ ሁሉም ተሳትፈዋል ብለዋል፡፡
የምክክሩ ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ፤ ኮሚሽኑ በሀገር ደረጃ ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎች የማሰባሰብ ሂደት በሲዳማ ክልል እየተካሄደ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
በመጪው ቅዳሜ ደግሞ በ #ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት እንደሚጀመር ቃል አቀባዩ ነግረውናል፡፡
‘’እስካሁን አጀንዳ በተሰበሰበባቸው 3 ክልሎች በምክክሩ ያልተሳተፉ የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም’’ ያሉት አቶ ጥበቡ ታደሰ ይህም ምክክሩ በታሰበው ልክ እየሄደ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
‘’እየተደረጉ እና የተደረጉ የአጀንዳ ማሰብሰብ ሂደቶች ግልፅ አካታችና ከመንግስት ተፅዕኖም ነፃ ናቸው’’ ሲሉ ቃል አቀባዩ ነግረውናል፡፡
የምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ ትግል የተመለሱ ነገር ግን የምርጫ ቦርድን እውቅና ያላገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ጠይቀውናል ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments