top of page

ነሐሴ 23፣2016 - የአለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) ለስድስት ወራት ለ3.9 ሚሊዮን ዜጎች የምግብ አቅርቦት ድጋፍ የሚሆን የተጣራ በጀት መያዙን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 29, 2024
  • 1 min read

የአለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) ለስድስት ወራት ለ3.9 ሚሊዮን ዜጎች የምግብ አቅርቦት ድጋፍ የሚሆን የተጣራ በጀት መያዙን ተናገረ፡፡


ከነሐሴ እስከ መጪው ወር ድረስ 3.9 ሚሊዮን ለሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን 33,400 ሜትሪክ ቶን እህል ለማከፋፈል ከ278 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዲሁም #ጥሬ ገንዘብን መሰረት በማድረግ ደግም በጥቅሉ 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለድጋፍ መመደቡን ሰምተናል፡፡


በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይና በሶማሌ ክልል የምግብ እጥረት ለገጠማቸው 1.7 ሚሊዮን ሰዎች 19,800 ሜትሪክ ቶን እህል በዓይነት እንዲሁም 973,000 ዶላር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እሰጣለሁ ሲልም #WFP ተናግሯል፡፡


የምግብ ፕሮግራሙ በመሬት መናድ ምክንያት በጎፋ የደረሰውን ጉዳት መሰረት በማድረግ ከ1,800 ለሚበልጡ ሕፃናት እድሜአቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆናቸው የገንቢ ምግብ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግሯል፡፡


የምግብ ፕሮግራሙ በስደተኛ ካምፖች እና የሀገር ውስጥ #ተፈናቃዮች ለሆኑ በርካታ ዜጎችም በ2024 አገልግሎት ሲሰጥ ነበር ተብሏል፡፡




የኔነህ ሲሳይ

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page