top of page

ነሐሴ 23፣2016 - ''በግጭት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል'' የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

  • sheger1021fm
  • Aug 29, 2024
  • 1 min read

በግጭት ምክንያት የወደሙ እስከ 200 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተናገረ፡፡


እነዚህ #ትምህርት_ቤቶች ወደ ነበሩበት ለመመለስ ክልሉ በ2017 የትምህርት ዘመን ለመስራት አቅዷል ተብሏል፡፡


የቤኒሻንጉል ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ምትኩ ዘነበ እንዳሉት በመጪው የትምህርት ዘመን የወደሙት ትምህርት ቤቶች ጥራታቸው ጠብቆ ለመገንባት የፋይናንስ ማፈላለግ ስራ ክልሉ ለመስራት አቅዷል፡፡


አሁን ላይ የአካባቢው ነዋሪ ባለው አቅም ልክ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ለመማር ማስተማር እያዋለ ነው ይላሉ አቶ ምትኩ፡፡

ነገር ግን ያለው የተማሪ ቁጥርና ትምህርት ቤቶች ቁጥር ባለመመጣጠኑ በአንድ ክፍል እስከ 70 ተማሪ በአንዴ ለመማር እየተገደደ ነው ብለዋል፡፡


ይህም #ለትምህርት_ጥራት_ችግር አንዱ ነው ያሉት የቤኒሻንጉል ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ ይህንን ለማስተካከል እያተኮርን ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡


በተለይም በቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተማሪዎች በቅተው ማንበብና መፅሐፍ አውቀው እንዲወጡ ለማድረግ ክልሉ እነዚህ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡


ከዚህም ባለፈ የመምህራን አቅም ለማሳደግ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው ያሉት አቶ ምትኩ ዘነበ ምክንያቱ ደግሞ #መምህራን ለትምህርት ጥራት ዋንኛው መነሻ ምክንያት ስለሆነ ነው ይላሉ፡፡


በክልሉ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶች በተሻለ ጥራት ለመገንባት ሁሉም ኢትዮጵዊ ሊተባበር ይገባል የተባለ ሲሆን ይህ እውን ከሆነ ተማሪዎች በተሻለ ክፍል ጥራት ያለው ትምህርት እንዲገኙ ያስችላል ሲሉ አቶ ምትኩ አሳስበዋል፡፡


በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page