top of page

ነሐሴ 23፣2016 - በደረሰው የውሃ መጥለቅለቅ ዙሪያ የፌዴራል መንግስቱና የዳሰነች ወረዳ እየተወዛገቡ ነው

  • sheger1021fm
  • Aug 29, 2024
  • 1 min read

በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት በደረሰው የውሃ መጥለቅለቅ ዙሪያ የፌዴራል መንግስቱና የዳሰነች ወረዳ እየተወዛገቡ ነው።


በኦሞ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በደረሰው የውሃ መጥለቅለቅ መውጣት ያልቻሉ ነዋሪዎችን ለማውጣት #የዳሰነች_ወረዳ የጀልባ እና የሄሊኮፍተር እገዛ ከፌድራሉ መንግስት ብጠይቅም ምላሽ አላገኘንም ማለታቸውን በቀደመ የወሬ ሰዓታችን ነግረናችሁ ነበር፡፡


በጉዳዩ ዙሪያ የፌዴራሉን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጠይቀናል፡፡


በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አታለል አቡሃይ በኦሞ ወንዝ ጉዳት የደረሰባቸውን ጨምሮ ለሌሎችም አካባቢዎች የእለት ደራሽ ምግብ እና ሌላውንም ድጋፍ እየላክን ነው ብለዋል፡፡

የዳሰነች ወረዳ በደረሰው የውሃ መጥለቅለቅ ተውጠው ያሉ ከ12,000 በላይ ሰዎችን ለማውጣት ለፌዴራሉ መንግስት የሄሊኮፍተርና የጀልባ ድጋፍ ጠይቀናል ቢልም የፌድራሉን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግን የዳሰነች ወረዳ ጥያቄ አላቀረበልንም ብሏል፡፡


ኮሚሽኑ #የሚትዮሮሎጂ_ትንቢያዎችን መሰረት በማድረግ ከሰኔ 2016 እስከ መስከረም 2017 ድረስ በጎርፍና የመሬት መንሸራተት የአደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ለይተን ለየአካባቢዎቹ አስተዳደሮች መረጃውን አድርሰናል የሚሉት አቶ አታለል አካባቢዎቹም ደቡብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያና ሰሜን ምስራቅ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡


ይህንን ተከትሎም በአብዛኞቹ አካባቢዎች አደጋዎቹ ተከስተዋል፤ ከኮሚሽኑም አስፈላጊ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡


ነገር ግን እንደ ደቡብ ኦሞ ያሉ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የከፋ አደጋ አለ ቢባሉም ከቦታቸው ለመነሳት ፍቃደኛ አይደሉም ይላሉ፡፡


የዳሰነች ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሳይ ሊበንም የውሃ መጥለቅለቅ አደጋው እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ነዋሪዎችን በአንድ ቦታ ላሰፈሯቸው ነዋሪዎች የእለት ደራሽ ምግብ እየደረሰ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ግን አደጋው የከፋ ቢሆንም አካባቢያችንን ለቅቀን ብንወጣ ከጎረቤት ኬንያ ያሉ አርብቶ አደሮች ይሰፍሩበታል በሚል ስጋት ለቅቀው መውጣት አይፈልጉም ብለውናል፡፡


በውዝግቡ ምክንያት በውሃ ሙላቱ ተውጠዋል የተባሉት የዳሰነች ዙሪያ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል፡፡

ቀደም ተብለው የተሰሩ ተያያዥ ዘገባዎችን ለማድመጥ




ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page