top of page

ነሐሴ 24፣2015 - በቤንዚን እና በነጭ ናፍጣ  የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ


ለ1 ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ይፋ አድርጓል።


በዚህም በምርቶቹ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።


በዚሁ መሠረት፦


በሊትር 69.52 ብር የነበረው ቤንዚን በ74.85 ብር ይሸጥ ተብሏል።


በሊትር 71.15 ብር ይሸጡ የነበሩት ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲን 76.34 ብር ሆነዋል።


የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 3.23 ጨምሮ 68.58 ብር ሆኗል።


ቀላል ጥቁር ናፍጣ ሊትሩ 62.22 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ 61.07 ብር ሆኗል።


ላለፉት 4 ወራት በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን የጠቀሰው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተናግሯል።


ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page