top of page

ነሐሴ 22፣2016 - በአማራ ክልል በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በርካታ ሰዎች እርዳታ ጠባቂ ለመሆን ተገደዋል

  • sheger1021fm
  • Aug 28, 2024
  • 1 min read

በአማራ ክልል በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በርካታ ሰዎች እርዳታ ጠባቂ ለመሆን ተገደዋል፡፡


በሰሞኑ የመሬት መንሸራተት በሰሜን ጎንደር ዞን 3,000 ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡


በዋግኽምራ ደግሞ በድርቅ ምክንያት ከ400,000 በላይ ሰዎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል፡፡


የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን በበኩሉ ለችግር የተጋለጡት አስቀድሜ ዝግጅት አድርጌያለሁ ብሏል፡፡


በዚህም 45,000 ኩንታል የመጠባበቂያ እህል ክምችት መኖሩንም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡


ይሁንና በክልሉ የቅደመ መከላከል ስራ ቢሰራም በስምንት ዞኖች በ34 ወረዳዎች 400,000 ሰዎች ለአደጋ እንደሚጋለጡና ከእነዚህ ውስጥ 28,000 ሰዎች እንደሚፈናቀሉ ታሳቢ አድርገን የመጠለያና የምግብ፣ የመድሃኒት፣ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ለሟሟላት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡



ማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page