top of page

ነሐሴ 22፣2016 - በባህላዊ ህክምና የሚደረጉ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ህክምናዎች በርካቶችን ለሞት እና ለከፋ አካል ጉዳት እየዳረጋቸው መሆኑን ጥናት አሳየ



በባህላዊ ህክምና የሚደረጉ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ህክምናዎች በርካቶችን ለሞት እና ለከፋ አካል ጉዳት እየዳረጋቸው መሆኑን ጥናት አሳየ።


ጥናቱን ያካሄደው በኢትዮጵያ #የአጥንት_ህክምናና የአደጋዎች ህክምና ስፔሻሊስቶች ብሔራዊ ማህበር ውስጥ ‘’BOSAD’’ የተሰኘው የባለሞያዎች የጥናት ቡድን ነው።


ጥናቱም በ6 ክልሎች የተካሄደ ሲሆን በ8 የተለያዩ የህክምና ተቋማት ላይ ያተኮረ መሆኑንም ሰምተናል።


በተለይ በልጆች ላይ የሚስተዋሉ የመውደቅ #አደጋ የዚሁ ችግር ሰለባ መሆናቸውም በጥናቱ ተመላክቷል።


በጥናቱ እንደተመለከተውም አብዛኞቹ የችግሩ ሰለባዎች እና የባህል ህክምናን እንደ ብቸኛ አማራጭ እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው በኢኮኖሚ አቅም ማነስ፣ ከአመለካከት ወይንም ከግንዛቤ ክፍተት እና በዘርፉ ላይ ግልጋሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ተደራሽ ባልሆኑበት የገጠር አካባቢ መሆኑም ተነግሯል።


#BOSAD የባለሞያዎች የጥናት ቡድን ይህንን ጥናት ሲያካሂድ የባህል ህክምናን የአሰራር ሂደት በማዘመን ተገቢውን ህክምና ለታካሚዎች እንዲሰጥ በማለም እንደሆነም ሰምተናል።


በጤና ሚኒስቴር በኩል በባህላዊ ህክምና ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶች ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እና መሰል የአሰራር ሂደቶችን ለመቀየር በቅርቡ በሚወጣው የጤና አዋጅ ላይ የህግ ማዕቀፍ እንደሚካተትበትም ሰምተናል፡፡



ፍቅሩ አምባቸው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page