top of page

ነሐሴ 22፣2016 - በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ ተናገረ

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ማረጋገጡን ተናገረ፡፡


ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1989 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 1999 ዓ ም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስረድቷል።


የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዘረፋ፣ በቅሚያ፣ በሌብነት፣ በቤት ሰብሮ ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ ተችሏል ብሏል።

ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣ 6 ቅምያ ወንጀል፣ 3 ሌብነት ወንጀሎች፣ 3 ሰው መግደል ወንጀል፣ 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣ ከእስር ማምለጥ ወንጀል እና አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች ያሉበት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አረጋገረጫለሁ ብሏል፡፡


ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ተገንዝቤያለሁ ሲል ፖሊስ ተናግሯል ።


እንደገና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት በጦር መሣሪያ የታገዘ የዘረፋ፣ ከአስር ቤት የማምለጥና በሌብነት ወንጀል የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጠት ያስተላለፈት መሆኑን የፖሊስ የምርመራ ማህደር አመላክቷል።


ተጠርጣሪው በውሳኔው መሠረት ማረሚያ ቤት የገባው ይግባኝ ጠይቆ ሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተቀየረለት ቢሆንም በድጋሚ ይግባኝ በማለቱ ቅጣቱ ወደ 25 ዓመት ተቀንሶለት ለ17 ዓመታት በማረሚያ ቤት ከቆየ በኋላ በይቅርታ መፈታቱን ፖሊስ ጠቅሷል፡፡

Comments


bottom of page