top of page

ነሐሴ 22፣2016 - ለ24,000 የቴክኒክና ሞያ አሰልጣኝ መምህራን ስልጠና መስጠት ዛሬ ተጀምሯል

በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የአሰልጣኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ ይረዳል የተባለ ስልጠና ለ24,000 የቴክኒክና ሞያ አሰልጣኝ መምህራን ስልጠና መስጠት ዛሬ ተጀምሯል፡፡


ስልጠናው ከዛሬ ነሃሴ 22 አስከ ጳጉሜ 3 የሚቆይ ሲሆን ‘’ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት’’ በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚሰጥ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


በዚህም በ17 የስልጠና ማዕከላት 24,000 የሚጠጉ የቴክኒክና ሞያ አሰልጣኞች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡


‘’ይህ ስልጠና ሰልጣኞች ብቻ ሳይሆኑ ከቴክኒክ እና ሞያ የሚወጡ ተማሪዎችም ብቁ እና ወቅቱን የሚመጥን ክህሎት ኖሯቸው እንዲወጡ ይረዳል’’ ሲሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page