በዚህም ምክንያት ተቀብረው ያሉ 6 አስከሬኖች ለማውጣት መቸገሩን የጠለምት ወረዳ ነግሮናል፡፡
የመሬት መንሸራተቱ ተከስቶ የነበረው አርብ ነሃሴ 17 ሲሆን በዚህም ምክንያት የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጠለምት ወረዳ የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው ዘነበ ተናግረዋል፡፡
ሟቾቹን ለማውጣት በሚደረገው ጥረት ዳግመኛ የመሬት መንሸራተቱ ተከስቶ 7 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ያሉት ኃላፊው አሁንም ድረስ የመሬት መንሸራተቱ ሊቆም አልቻለም ብለዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ሟቾቹ ከተቀበሩበት ለማውጣት አልቻልንም፤ የመሬት መንሸራተት አደጋ በቤቶች በቤት እንስሳት እና በ30 ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት አስከትሏል ይላሉ፡፡
በዚህ የመሬት መንሸራተት ምክንያት 448 አባወራዎች ከአካባቢያቸው እንዲነሱ ተደርጓል ያሉት አቶ ግዛው ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስ በተቻለ አቅም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች ዞኑ አሁን ላይ የአቅሙን እየረዳ ነው ያሉ ሲሆን መጠለያ እና አልባሳት ለሁሉም ባይሆንም የተገኘው ያህል ወደ ወረዳው እየተላከ መሆኑን ነግረውናል፡፡
ክረምት ከመሆኑ አኳያ የተፈናቀለው የሰው ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ አፋጣኝ እርዳታ ከሁሉም ይጠበቃል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በ2016 የክረምት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንሸራተት በተደጋጋሚ እየተከሰተ ሲሆን በዚህም ምክንያት የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ይገኛል፡፡
የዘርፉ ባለሙያዎች ይህ የመሬት መንሸራተት በቀጣይ የክረትም ወቅቶች ሊቀጥል እንደሚችል ያስጠነቀቁ ሲሆን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እየመከሩ ነው፡፡
በረከት አካሉ
Comments