‘’በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ የሀገራችንን አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ወገኖቻችን በመጎዳታቸው ማዘናቸውን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
‘’ለብዙ ዘመናት ተፈጥሮን ባለመከባከባችን አሉታዊውን ውጤት አያየ ነው’’ ያሉም ሲሆን ‘’የአረንጓዴ ዐሻራ ስራን ችግሩን የመፍቻ ቁልፍ መፍትሔ’’ እንደሆነም ተናግረዋል።
‘’በተለያዩ የሀገራችንን አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው፤ ሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ መመሪያ ተሰጥቷል’’ ብለዋል።
በአደጋዎቹ ለተጎዱ ሰዎች፤ ማኅበረሰቡም በተቻለው ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመሬት መንሸራተት በጎርፍ በተለይ በጎፋ ዞን፣ በሰሜን በጎንደር፣ በዳሰነች ወረዳ ፣ በስልጤ ዞን፣ በወላይታ ዞን እና በካፋ ዞን ሰዎች መሞታቸው እና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments