ነሐሴ 20፣2016 - የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያው እንደሚባለው በጥቁር እና በትይዩ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥብበ አልያም ማስቀረት ይችል ይሆን?
- sheger1021fm
- Aug 26, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ ከአንድ ወር በፊት የውጭ ምንዛሪ ገበያ መር እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ይህ ማሻሻያ በጥቁር ገበያ እና በትይዩው መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ያጠባል አልያም እንደሚያስቀር ታምኖበታል፡፡
እውነት ይህ ማሻሽያ እንደሚባለው በጥቁር እና በትይዩ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥብበ አልያም ማስቀረት ይችል ይሆን?
በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር የፖሊሲ ትንተና እና የጥናት ዳይሬክተር የሆኑትን ደግዬ ጎሹን(ዶ/ር) ጠይቀናል፡፡
እሳቸው የውጪ ምንዛሪው ገበያ መር እንዲሆን መወሰኑ በጥቁር ገበያ እና በትይዩ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት እንደሚያጠብ ያስረዳሉ፡፡
ምክንያቱ ደግሞ ‘’ከዚህ በፊት ወደ ጥቁር ገበያ የሚገፉ ምክንያቶች መለስ ስላገኙ ነው ሲሉ’’ አስረድተዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments