top of page

ነሐሴ 20፣2016 - የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች ስራ መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች ስራ መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።


ስራ መጀመራቸውን የተነገረው እነዚህ ተርባይኖች ለግድቡ 3ኛ እና 4ኛ ተርባይኖች ናቸው።


ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አስረድተዋል።


የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል እንደቀጠለም ጠቅሰዋል።

''የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2,800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል'' ብለዋል።


''የግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠር፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ፣ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል'' ሲሉም ጠቅሰዋል።


''ይህ የተመዘነና የተመጣጠነ የውሃ ልቀት ግብርናን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን፣ በቀጠናው ያለ የሀብት አጠቃቀም ምጣኔን ለማጎልበት ጠቃሚ ነው'' በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page