top of page

ነሐሴ 20፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች


የብራዚሏ ሳኦ ፓውሎ ግዛት በሰደድ እሳት እየተፈተነች ነው፡፡


ቃጠሎው እስከ ትናንት የሁለት ሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


30 ከተሞች በሰደድ እሳቱ መዛመት አደጋው ያሰጋቸዋል ተብለው ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡


በግዛቲቱ በመዛመት ላይ የሚገኘው የሰደድ እሳት የትራፊክ ወዲህ ወዲያውን እያወከ ነው ተብሏል፡፡


ደረቅ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ለሰደድ እሳቱ መዛመት በዋነኛ ምክንያትነት ቀርቧል፡፡


የግዛቲቱ ማእከል ሳኦ ፓውሎም በሰደድ እሳት ጭስ ጭጋግ መታፈኗ ተጠቅሷል፡፡


የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ከRSF ሀይል ጋር በጭራሽ አንደራደርም አሉ፡፡


የሱዳን መንግስት ጦር ከ RSF ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጋር ሲዋጋ ከአመት ከ4 ወራት በላይ ሆኖታል፡፡


በአሜሪካ አመቻችነት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሰላም ንግግር ከተጀመረ ቆይቷል፡፡


አል ቡርሃን ግን ለመቶ አመታት ቢሆንም እዋጋለሁ እንጂ ከአርኤስኤፍ (RSF) ጋር በጭራሽ አልደራደርም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


በጄኔቫ ስዊዘርላድ የሱዳን የሰላም ንግግር ተጀምሯል ቢባልም የሱዳን መንግስት ጦር ተወካዮች ያልተኙበት ነው ተብሏል፡፡


RSF ግን ተወካዮቹን ወደ ጄኔቫ መላኩ ታውቋል፡፡


የጄኔቫው ንግግር በቅድሚያ በአገሪቱ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የማድረግ ዓላማ እንዳላው የአሜሪካ ድምፅ ፅፏል፡፡




ግብፅ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስራኤል ጦር እና የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ጠብ እንዲያበርዱ ተማፀኑ፡፡


የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ተመሳሳይ ጥሪ ማቅረባቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


የተባበሩት መንግስታት እና ግብፅ ስጋታችንን እወቁልን ያሉት የእስራኤል ጦር እና ሔዝቦላህን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ወሰን ተሻጋሪ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው፡፡


ነገሩ ወደ ከባድ አካባቢያዊ ግጭትነት ሊሸጋገር ይችላል ሲሉም በብርቱ አስጠንቅቀዋል፡፡


የእስራኤል ጦር እና የሔዝቦላህ ቁርቋሶ ወደ ሙሉ ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል የሚለው ስጋት የሰነበተ ነው፡፡


እስራኤልም ሆነች ሔዝቦላህ ከሀይል ተግባር እንዲታቀቡ ጥሪው ጎልቶ እየተሰማ ነው፡፡


የኔነህ ከበደ

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page