top of page

ነሐሴ 20፣2016 - ከአሜሪካ የመጡ ከ17 በላይ የልብ ህክምና ባለሞያዎች ነፃ የልብ ህክምና መስጠት ጀመሩ

ከአሜሪካ የመጡ ከ17 በላይ የልብ ህክምና ባለሞያዎች ነፃ የልብ ህክምና መስጠት ጀመሩ፡፡


ለሁለት ሳምንት የሚቆየው የህክምና ቡድኑ 70 የልብ ህሙማን ያክማል ተብሏል፡፡


‘’ኸርት አታክ ኢትዮጵያ’’ የተሰኘው  ግብረ ሰናይ ድርጅት መቀመጫው በአሜሪካ ጆርጅያ እንደሆነና ከዚህ ቀደምም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለ32 ህሙማን የቀዶ ህክምና ማድረጉን ተናግሯል፡፡

በአሁኑ ደግሞ ለ43 ህሙማን  የቀዶ ህክምና ማድረጉ እና ለሁለት ሳምንት በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማዕከል አገልግሎት እንደሚሰጥ ሰምተናል፡፡


ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ 1.3 ሚሊዮን  ዶላር የተገመተ ለህክምና የሚያገለግል መሳሪያ ይዞ መምጣቱን የኸርት አታክ ኢትዮጵያ መስራች መካከል አንዱ የሆኑት ተስፋዬ ተሊላ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡


‘’ከዚህ ቀደም ለበጎ አድራጎት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ነጮች ብቻ ናቸው አሁን ግን ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው እጅግ ደስ ብሎናል’’ ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ስራ አስፈጻሚ አቶ ህሩይ አሊ ናቸው፡፡



ማርታ በቀለ

Comentarios


bottom of page