ነሐሴ 2፣2016 - መንግስታዊ ያልሆኑ ረጂ ተቋማት አንዳንድ የክልል ከተሞች ላይ በስፋት ሲኖሩ ሌሎች አካባቢዎች ላይ ደግሞ እንደማይኖሩ ሰምተናል
- sheger1021fm
- Aug 8, 2024
- 1 min read
ነሐሴ 2፣2016
መንግስታዊ ያልሆኑ ረጂ ተቋማት በውሃ እና ኢነርጂው ዘርፍ የሚያደርጉት ድጋፍ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም ክልሎች መድረስ አለበት ሲል የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ረጂ ተቋማት አንዳንድ የክልል ከተሞች ላይ በስፋት ሲኖሩ ሌሎች አካባቢዎች ላይ ደግሞ እንደማይኖሩ ሰምተናል፡፡
ይህንን ፍትሃዊ ለማድረግ የሚሰሩ #ፕሮጀክቶች በእቅድ መተግበር አለባቸው ተብሏል፡፡
የሚደረጉት ድጋፎች የክልሉ የውሃ ቢሮ ሳያውቅ ወደ ክልሉ ፋይናስ እና የአደጋ ስጋት ቢሮ እንደሚገባና ይህ ደግሞ ከፍተኛ ለሆነ የገንዘብ ብክነት እንደሚዳርግ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Kommentarer