top of page

ነሐሴ 2፣2015 -ደም አፋሳሽ ግጭቶች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ


በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይና ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ፡፡


ግጭቶች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጥሪ ያቀረበው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ነው፡፡


ኮሚሽኑ ግጭቶች እንዲቆሙ፤ ልዩነት አለን የሚሉትን ሁሉ ለማቀራረብ እና ለማመሳከር ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ወቅታዊ ጉዳዮችን መሰረት አድርጎ ዛሬ ረፋድ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡


የኮሚሽኑ ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ የሀሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች መኖራቸውን አስታውሰዋል፡፡


ልዩነትና አለመግባባቶችን በሀገራዊ ምክክር ለመፍታት በተለያዩ አምስት ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡


ይሁንና በአማራ ክልል በቅርቡ የተከሰተውን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለው ግጭት የኮሚሽኑን ስራ አዳጋች አድርገውታል ብለዋል፡፡


ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸውን ኮሚሽኑ ይህን አስቸኳይ የሰላም ጥሪ ለማቅረብ ተገዷል ተብሏል፡፡


በመሆኑም የሚታዩ ግጭቶች ሁሉ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ቁመው ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


ለዚህም ባለድርሻ አካላትን በማቀራረብ የልዩነት አጀንዳዎችንም ሰብስቦ ለማወያየትና ለማመሳከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ኮሚሽኑ ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡



ትዕግስት ዘሪሁን




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Website: https://www.shegerfm.com/


Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

bottom of page