top of page

ነሐሴ 2፣2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ቀናት ወደ አማራ ክልል የሚደረጉ በረራዎችን ሰርዣለሁ አለ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች መሰረዙን ተናገረ፡፡


ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞች ወደፊት በፈለጉት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር እንደሚችሉና የተቆረጡ ትኬቶች ለአንድ ዓመት ያህል ያገለግላሉ በሏል፡፡


ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉ ደንበኞች ግን አቅራቢያቸው ወደሚገኙ የአየር መንገዱ የትኬት መሻጫ ቢሮዎች ወይንም የጉዞ ወኪሎቻቸው ጋር በመቅረብ መስተናገድ እንደሚችሉም ተናገሯል፡፡


አየር መንገዱ ለሚፈጠረው መጉላላት ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Website: https://www.shegerfm.com/


Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page