ባለፉት 6 ዓመታት 40 ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል ተባለ፡፡
በ2011 በተጀመረው ችግኝ የመትከል እቅድ 40 ቢሊዮን ችግኝ መተከላቸው ተነግሯል፡፡
ከተተከሉት 40 ቢሊዮን ችግኞች ውስጥ ለውበት፣ ለደን ለምግብና ለመኖ የሚያገለግሉ እንደሆኑ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
በተናንትናው እለትም 600 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ 615.7 ሚሊዮን ችግኝ መትከል እንደተቻለ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስረድተዋል።
29.1 ሚሊዮን ዜጎች በ318.4 ሄክታር በጂኦስፓሻል መረጃ በተገኘባቸው ስፍራዎች ላይ ችግኞችን ተክለዋል ተብሏል።
እስካሁን በመረጃ ቋት ከተመዘገበው ውጭ የተተከሉ ችግኞች መረጃ በተከታታይ ይነገራል ተብሏል።
ለመሆኑ ሀገሪቱ በየዓመቱ የምትተክላቸው ችግኞች እየጠጸደቁ ነው ወይ፤ ምንስ ለውጥ አመጡ?
ምንታምር ጸጋው
Comments