በትግራይ ክልል ለሚገኙ ወደ 200,000 የሚጠጉ የመንግስት ሰራተኞች እስካሁን የ17 ወር ውዝፍ ደመወዝ አልተከፈላቸውም ተባለ፡፡
ይህን ያለው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ነው፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ፀሐዬ እንባዬ ‘’በክልሉ ላሉ ጡረተኞች 17 ወር ወዝፍ ደሞዛቸው ተከፍሏቸዋል ያሉ ሲሆን ለፌዴራል እና ለክልል መስሪያ ቤት ግን ክፍያው አልተፈጸመላቸውም’’ ሲሉ ነግረውናል፡፡
137,000 የሚሆኑ የክልል ሰራተኞች በፌዴራል መንግስት እና በህወሃት መካከል ተደርጎ በነበረው ጦርነት ምክንያት የ17 ወር ውዝፍ ደመወዝ አልተከፈላቸውም በዚህም ምክንያት ሰራተኛው ለችግር ተጋልጧል ተብሏል፡፡
የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሰራተኞችን ጨምሮ የሌሌች በክልሉ ያሉ የፌዴራል መሰሪያ ቤት ሰራተኞች ደግሞ የ19 ወር ውዝፍ ደመወዝ አልተሰጣቸውም ሲል ጽህፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡
‘’ሰራተኛው ደመወዙ ተቋረጦበት በነበረበት ወቅት 17 ወር ሙሉ በዱቤ ነበር ቤት ተከራይቶ ሲኖር የነበረው አሁን ያን ልክፈል ቢል የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ አይደለም ዱቤ ለመክፈል ከወር ወር እንኳን የሚያቆይ አይደለም’’ ሲሉ ኃላፊው ነግረውናል፡፡
ኃላፊው ‘’በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲያነጋግረን ደብዳቤ ብንፅፍም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም’’ ብለዋል፡፡
መንግስት ሰራተኛው ያለበትን ችግር ተረድቶ ለጡረተኞች የፈፀመውን ውዝፍ ክፍያ ለመንግስት ሰራተኞችም እንዲከፍላቸው የፅ/ቤቱ ሀላፊ ጠይቀዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments