top of page

ነሐሴ 15፣2016 - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ህይወቷ ላለፈው ህፃን ሄቨን ወላጅ እናት የመኖሪያ ቤት መስጠቱን ተናገረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ህይወቷ ላለፈው ህፃን ሄቨን ወላጅ እናት የመኖሪያ ቤት መስጠቱን ተናገረ።


ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል ተብሏል::


"ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሞያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን" ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል፡፡

"የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው’’ ያሉት ከንቲባ አዳነች ‘’የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም" ሲሉም አስረድተዋል፡፡

Opmerkingen


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page