ይህም ወደ ውጪ ሀገር ጉዞ ለሚያደርጉ የባንኩ ደንበኞች፣ የኤምባሲዎች እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኞች ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳያስፈልጋቸው በየትኛውም የዓለም ክፍል ክፍያ መፈፀም የሚያስችላቸውን ነው ተብሏል፡፡
የባንኩ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ወጋገን ባንክ ከቪዛ ጋር በመተባበር ያስጀመረው አገልግሎት የባንኩ ደንበኞች ወደ ውጭ ሀገር በሚጓዙበት ወቅት ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳያስፈልጋቸው ባንኩ ያዘጋጀላቸውን የዓለም አቀፍ የቪዛ ካርድ በመጠቀም በየትኛውም የዓለም ሀገራት በሚገኙ የኤቲኤም እና የክፍያ መፈፀሚያ(POS) ማሽኖች ገንዘብ ማስተላለፍ እና ክፍያን መፈፀም የሚያስችል መሆኑ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አገልግሎቱ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተስፋፋ በመጣው ኢ-ኮሜርስ አማካኝነት ግብይት መፈፀም እንዲሁም በውጪ ሃገር ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጲያውያን ዳያስፖራዎች ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻችው ተጨማሪ የዲጂታል ሃዋላ አማራጭ በመሆን ከየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ሰዓት ደህንነነቱ በተጠበቀ መንገድ በፍጥነት ገንዘብ መላክ እንደሚያስችል አቶ ሰለሞን ጠቅሰዋል፡፡
የቪዛ ካንትሪ ሃላፊ አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው ቪዛ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ አገሮች ላይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የፋይናንስ ሴክተር ላይ ከፍተኛ እምርታ ለማምጣት የተለያዩ አካታች፣ ፍታሃዊ እና ዘላቂ ፕሮጀክቶች ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አቶ ያሬድ አክለውም የቪዛ ካርድ ከወጋገን ባንክ ጋር በመሆን የተለያዩ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ወጋገን ባንክ በአሁኑ ወቅት የተከፈለ ካፒታሉ ከብር 5 ቢሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉ ከብር 10 ቢሊዮን አድጓል ተብሏል፡፡
438 ቅርንጫፎቹች፣385 የኤቲኤም እና 430 የክፍያ መፈፀሚያ (ፓስ) ማሽኖች፣ በ4,800 ወኪሎች እንዲሁም የኢንተርኔት እና ሞባይል ባንኪንግ የዲጂታል አገልግሎቶችን እየሰጠው እገኛለሁ ብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments