top of page

ነሐሴ 15፣2016 - በኢትዮጵያ ወደ ወጭ የሚላኩ ምርቶች በቋሚነት የሚተዋወቁበት የኤግዚቢሽን ማዕከል ተዘጋጀ

በኢትዮጵያ ወደ ወጭ የሚላኩ ምርቶች በቋሚነት የሚተዋወቁበት የኤግዚቢሽን ማዕከል ተዘጋጀ።


ማዕከሉ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ የተገነባ ሲሆን የፊታችን እሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ሚኒስቴሩ ተናግሯል።


የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ጉዳዩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ማዕከሉ ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ዘርፍ አሉኝ የምትላቸውን ምርቶቿን የምታሳይበት ነው ብለዋል።


ከማዕከሉ ምርቃት በተጨማሪ በዚሁ እለት ማለትም ከነሃሴ 19 እስከ 23፣2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ፣ የሃገር ውስጥ ምርቶች በቀነሰ ዋጋ የሚገበያዩበት የንግድ ትርኢት በሚኒስቴሩ ተዘጋጅቷል።


የኢትዮጵያን ይግዙ በሚል የተሰናዳውን የንግድ ትርኢት ሚኒስቴሩ በራሱ ህንፃ ላይ ባስገነባው ኤግዚብሽን ማዕከል ይከናወናል ተብሏል።

ኤግዚቢሽኑን ማዘጋጀት ያስፈለገው የሃገር ውስጥ ምርቶችን በብዛትም በጥራትም በማቅረብ፣ ሸማቹ ወደ ሃገር ውስጥ ምርቶች እንዲያዘነብል በማድረግ ከውጭ የሚገባውን መቀነስ መሆኑን ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ጠቁመዋል።


ሁሉም ዓይነት የሃገር ውስጥ ምርቶች በቀነሰ ዋጋ የሚሸጡበት ነው በተባለው ኤግዚብሽን ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ይቆያል፤ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በመሄድ መሸመት ትችላላችሁ ተብላችዋል።


ምንታምር ፀጋው

Comments


bottom of page