በየዓመቱ 700 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይገኝበታል በሚባለው የአውት ሶርሲንግ የስራ መስክ ላይ ኢትዮጵያም ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በስፋት ልታሰማራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ስራውን ለመስራት እንቅፋት ናቸው የተባሉ የአሰራር ሥርዓቶች ቀርተው ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርም ተጠይቋል፡፡
አንድ ተቋም አልያም ድርጅት በራሱ ሰራተኞች መስራት የሚችለውን ስራ አነስ ባለ ክፍያ በሌሎች ሰራተኞች የማሰራት ሂደት አውት ሶርሲንግ እንደሚባል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ይህ የስራ መስክ ምንም ዓይነት የጉልበት ንክኪ ሳይኖረው አሰሪው ድርጅት ጋርም ሳይኬድ በኢንተርኔት የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ የስራ መስክ አሜሪካ በዓመት ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ታገኛለች የተባለ ሲሆን ከአፍሪካ ድግሞ ደቡብ አፍሪካ ፤ ግብጽ እና ኬኒያ ከመስኩ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ካዝናቸው ያስገባሉ፡፡
ሶስቱ የአፍሪካ አገራት እያንዳንዳቸው ኢትዮጵያ አምርታ ወደ ውጭ ልካ ከምታገኛው ገቢ የውጭ ገቢዋ በእጥፍ የሚበልጥ አልያም የሚስተካከል ያገኛሉ ተብሏል፡፡
ይህ የተባለው የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የአውት ሶርሲንግ ማህበር ጋር ባሰናደው መድረክ ላይ ነው፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments