top of page

ነሐሴ 15፣2016 - በትግራይ ክልል ያሉ ፖለቲካዊ ልዩነቶች ለፀጥታ ችግር ስጋት እንዳይፈጥሩ እየተሰራ መሆኑን ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ

  • sheger1021fm
  • Aug 21, 2024
  • 1 min read

በትግራይ ክልል ያሉ ፖለቲካዊ ልዩነቶች ለፀጥታ ችግር ስጋት እንዳይፈጥሩ እየተሰራ መሆኑን ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ፡፡


የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ #የሰላምና_ፀጥታ_ቢሮ ምክትል ፕሬዘዳንት የሆኑት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በወቅታዊ የፖለቲካና የፀጥታ ጉዳይ እና ተፈናቃዮችን በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡


በመግለጫው ''ፖለቲካዊ የሀሳብ ልዩነቶች ጤናማ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ጠቅሰው ለፀጥታ ችግር ምክንያት እንዳይሆን ግን እየሰራን ነው'' ማለታቸውን ትግራይ ቲቪ ዘግቧል፡፡


የሀሳብ ልዩነቶች ያሏቸው ፖለቲከኞችም ልብ ገዝተው ልዩነቶቻቸውን በፖለቲካዊ አግባብ እንዲፈቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡


የፀጥታ አካላትም በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ ሆነው ለህዝብ ደህንነት እንዲቆሙ ጠይቀዋል ተብሏል፡፡


የሀሳብ ልዩነቶች የተንፀባረቁበትና በመቀሌ ከተማ የተካሄዱ የተለያዩ ጉባኤተኞችም በሰላም አንዲጠናቀቁ ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል ላሏቸው ህግ አስከባሪ አካላትም ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡


አያይዘው ተፈናቃዮችን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ተፈናቃዮች በተመለሱባቸው አካባቢዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ እና የሚያስተዳድራቸውን አካል በነፃነት እንዲመርጡ ለማስቻል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት ጌታቸው ረዳ ተፅፎ ለተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች በተላከው ደብዳቤ ያለ ፅህፈት ቤታቸው እውቅና ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡


በተያዘው የክረምት ወቅት ተፈናቃዮችን ለመመለስ ፣ የኮሌራ ህመምን ለመከላልና ተያያዥ ህዝባዊ መንግስታዊ ስራዎችን ለመከወን በትኩረት እንደሚሰራ መሆኑን በደብዳቤያቸው ጠቅሰዋል፡፡


በሂደቱም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እውቅና ውጭ የሚካሄዱ ስብሰባዎች እውቅና እንደማይሰጣቸው በደብዳቤያቸው አሳስበዋል፡፡


ስብሰባዎችን ሲያካሂዱ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲያሳውቁ በደብዳቤ የተጠየቁት የክልሉ ሁሉም የወረዳ አስተዳደሮች፣ ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮችና የወረዳ ምክር ቤቶች ናቸው፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page