top of page

ነሐሴ 14፣2016 - የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ 79,000 ሰዎችን አፈናቀለ፡፡

ከሰሞኑም እየጣለ ባለው #ከባድ_ዝናብ ወንዙ ሞልቶ በዙሪያው ያሉ ወረዳዎችን በሙሉ መጥለቅለቃቸውንና በዚህም በስፍራው ያሉ 79,000 ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሃቴ ለሸገር ተናግረዋል፡፡


ነዋሪዎቹ በ2016 ዓ.ም መግቢያ ላይ በመሰል #የጎርፍ_አደጋ ከቀያቸው ተፈናቅለው ባሉበት ስፍራ ከሰሞኑ የተከሰተው የኦሞ ወንዝ ሙላት ዳግም እንዳፈናቀላቸውና የእለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡


የሰሞኑ የአየር ትንቢያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የክረምቱ ዝናብ እንደሚጠነክር ነው የሚሉት አቶ ታደለ ዝናቡ በዚሁ ከቀጠለ እና የወንዙ ውሃ ማስተንፈሻ ካላገኘ በቅርብ እርቀት ላይ ሚገኘውን የዞኑን ዋና ከተማ ኦሞራቴን ሙሉ ለሙሉ ሊያወድመው ይችላል የሚል ስጋታቸው ነግረውናል፡፡

የፌድራል መንግስቱንም ለአካባቢው ትኩረት ሰጥቶ ዘላቂ መፍትሄ ይፈልግልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


#የኢትዮጵያ_ቀይ_መስቀል_ማህበር የደቡብ ኦሞ ዞን ቅርንጫፍም አደጋው ተከትሎ ያለውን ስጋት ለመቅረፍ የቱርካና ሃይቅና የኦሞ ወንዝ የኦሞራቴን ከተማ እንዳያጠፋት ለመከላከል የመገደብ ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡


#የኦሞ_ወንዝ በሚያስከትለው መጥለቅለቅ የአካባቢው ስነምህዳር ተቀይሯል፤አርሶ መብላት አልተቻለም፤እንሰሳት በወንዙ ይወሰዳሉ ያሉት ሃላፊው በዘላቂነት የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/ax239urw


ምንታምር ፀጋው

Comments


bottom of page