ነሐሴ 14፣2016 - የተደረገው ማሻሻያ ኤክስፖርቱን ዘርፍ ሊያበረታታው እንደሚችል ተነግሯል
- sheger1021fm
- Aug 20, 2024
- 1 min read
ኢትዮጵያ ቡናዋንም፣ ወርቁንም፣ ጫቷንም ለውጭ ገበያ አቅርባ የምታገኘው ገቢ የነዳጅ ወጪዋን እንኳን አልሸፈነም፡፡
በአንፃሩ ሀገሪቱ ለገቢ ምርቶች ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታወጣለች፡፡
በቅርቡ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ይህንን ከፍተት ያስተካክለዋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረው ነጋዴውን በከፍተኛ ጫናውስጥ የከተተ ነበር፡፡
ይህ የተደረገው ማሻሻያ ኤክስፖርቱን ዘርፍ ሊያበረታታው እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ነጋዴው ማህበረሰብ የተደረገውን ማሻሻያ በበጎ ጎኑ እንደተመለከተ የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ወይዘሮ መሰንበት ሽንቁጤ ነግረውናል፡፡
በለውጡ የሚያንገራግጩ ነገሮች ቢኖሩም ከሌሎች ሀገሮች ልምድ መውሰድ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
ነጋዴው ግራ እንዳይጋባ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ፕሬዝዳንቷ አስረድተዋል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments