top of page

ነሐሴ 14፣2016 - የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች መንግስት የደሞዝ ማሻሻያ አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች መንግስት የደሞዝ ማሻሻያ አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡


ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰን አለበት በሚል የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌድሬሽን በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡


መንግስት ለራሴ ሰራተኞች #የደመወዝ_ጭማሪ አደርጋለሁ ቢልም ከፍተኛ የሆነ እና ብዛት ያለው የማህበረሰብ ክፍል በግሉ ዘርፍ ተሰማርቷል ይህ የደመወዝ ጭማሪ እነሱንም ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ያሉት የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ደግዬ(ዶ/ር) ጎሹ ናቸው፡፡


መንግስት ደመወዝ እጨምራለሁ ማለቱ ተገቢ ሆኖ ሳለ የገበያ ሁኔታ እና ህገወጥ ነጋዴዎችን በቋሚነት መቆጣጠር ካልቻለ ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችል እና ከሚጨመርለት ደመወዝ በላይ ሊያወጣ እንደሚችል የነገሩን ደግሞ #የኢትዮጵያ_ሰራተኞች_ማህበራት_ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ናቸው፡፡


መንግስት ለነጋዴው ማህበረሰቡ የዋጋ ተመን እንዲያወጣለት ሳይሆን የተጋነነ ዋጋ እንዳያወጣ በቂ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ አለበት ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡


የተደረገው ማሻሻያ መልካም ጎን አለው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለሀብቶች ለሰራተኛው የስራ እድል ከመፍጠር ጋር የተሻለ የሆነ ነገሮች ይታይናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page