top of page

ነሐሴ 14፣2016 - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን የጋዜጠኝነት ትምህርትን ለማስተማር የሚረዳ የማስተማሪያ ክፍል አስመረቀ

የጋዜጠኝነት ትምህርትን በተሻለ መንገድ ለማስተማር የሚረዳ የማስተማሪያ ክፍል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን አስመረቀ


የማስተማሪያ ክፍሎቹ አሁን ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማሉ የተባለ ሲሆን ተማሪዎች በተሻለ መንገድ ተግባር ተኮር ትምህርት እንዲቀስሙ ይረዳል ተብሏል፡፡


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ስነ ተግባቦት ትምህርት ክፍል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብድራህማን ዲኖ የሚዲያ ቴክኖሎጂ በየጊዜው በፍጥነት እየተቀያየረ ነው ተማሪዎችም በዛው መንገድ ማዘጋጀት ካልተቻለ ከባድ ፈተና ይሆናል ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የተዘጋጁት የመማሪያ ክፍሎች ተማሪዎችን በተሻለ መንገድ ትምህርታቸው በተግባር እንዲማሩ ይረዳል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በተለይም ሀሰተኛ መረጃ በምን መንገድ መለየት እንዳለባቸው እንዲያውቁ ይረዳል ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋዜጠኞች ለማህበረሰቡ ተጣራ እና እውነተኛ መረጃ ማቅረብ አለባቸው አሁን ያለው ቴክኖሎጂ በየጊዜው ተቀያያሪ ነው ያሉ ሲሆን ተማሪዎችም ይህንን ተገንዝበው ነው ሊዘጋጁ የሚገባው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


አሜሪካ እንዲህ ያለውን ድጋፍ የምታደርገው በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለው ትስስር የመለጠ የጠበቀ እንዲሆን ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጀመረው እራስ ገዝ የመሆኑ ስራ እያገዘ ነው ያሉ ሲሆን በተለይም ልምድ ያላቸው አማካሪዎች ከአሜሪካ እና ከተለያዩ ሀገራት እያስመጣ እንዲያግዙ ያደርጋል፡፡


ይህኛው ድጋፍም የጋዜጠኝነት ትምህርት በተሻለ መንገድ ለመስጠት ና ብቁ ባለሙያ ለማፍራት ያግዛል ብለዋል፡፡

ለስራዉ የአሜሪካ ኤምባሲ 500,000 ዶላር ማውጣቱንም ሰምተናል፡፡


በረከት አካሉ

Comments


bottom of page