በኢትዮጵያ ከ120,000 በላይ ታራሚዎች እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ከ500,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በዓመት ውስጥ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያልፋሉ፡፡
ከእነዚህም መካከል 15 በመቶ ገደማዎቹ እድሜያቸው ከ14 እስከ 18 የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ጥናት አሳይቷል፡፡
ከአጠቃላይ 120,0000 በላይ ታራሚዎች ውስጥ 4 በመቶዎቹ ሴቶች እንደሆኑም የተመድ መረጃ ተናግሯል፡፡
ታዲያ ጥፋት ተገኝቶባቸዋል ተብለው ወደ ማረሚያ ቤቶች የገቡ ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? ሀገሪቱ ታራሚዎችን አንጻ በማውጣቱ ምን ያህል እየተሳካላት ነው?
በማረሚያ ቶች እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችስ ምንድናቸው? የሚመለከታቸውን የመንግስት ሀላፊዎችንና በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡
ባለፉት 2 ዓመታት 4 ጥናቶችን በማረሚያ ቤቶች ዙሪያ አድርገናል የሚሉት የሴንተር ፎር ጀስቲስ(Center For Justice) የተሰኘ ድርጅት ዳይሬክተር ኩምሳ ጉታታ፤ ''በኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች መሰረታዊ የሚባሉ የአገልግሎት ክፍተቶች እንዳሉ'' ያስረዳሉ፡፡
ከእነዚህም ዉስጥ የእስር ቤት ጥበት አንዱ እንደሆነ የሚያነሱት ዳይሬክተሩ ታራሚዎች ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ ናቸው ብለዋል፡፡
በተጨማሪ ''ታዳጊ ታራሚዎች ከአዋቂዎች ጋር እንድላይ በመሆናቸው ከመታረም ይልቅ ሎሎች ወንጀሎችን የሚሰሩበት መንገድ እንደሚማሩ'' እንስተዋል፡፡
ጥናቶች እንዳሳዩት፤ የምግብ እጥረት በማረሚያ ቤቶቹ የሚታየው ሌላኛው ችግር ነው፡፡
ቃሊቲ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ ድሬዳዋን ጨምሮ በፌደራል ደረጃ በሚተዳደሩት 6 ማረሚያ ቤቶች የአንድ ታራሚ የቀን የምግብ በጀት 35 ብር ነው፡፡
በክልሎች ስር በሚተዳደሩት ማረሚያ ቤቶች፤ የምግብ በጀት እንደየ ክልሎቹ የሚለያይና ሰፊ ልዩነት የሚታይበትም እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ለአብነትም ካሉ ክልሎች ዝቅተኛ የቀን በጀት ይመድባል የተባለው የጋምቤላ ክልል ሲሆን ለአንድ ታራሚ በቀን ለምግብ የሚመድበው 22 ብር ነው ተብሏል፡፡
የሲዳማ ክልል 59 ብር በመመደብ ከፌደራልም ሆነ ከክልሎች ከፍተኛው መሆኑ በጥናቱ ታውቋል፡፡
22 እና 35 ብር መመደቡ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር የማይጣጣም ስለሆነ መሻሻል እንደሚገባው አቶ ኩምሳ ተናግረዋል፡፡
ከወላጆቻቸው ጋር ወደ እስር ቤት የሚገቡ ህፃናት ጉዳይም አሳሳቢ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ7,000 በላይ ህጻናቶች በማረሚያ ቤት ወስጥ ያልፋሉ ተብሏል፡፡
በአሁን ወቅትም 1,400 ህፃናት በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡
ወላጆቻቸው ባጠፉት ጥፋት ምክንያት ማረሚያ ቤት የሚገቡት እነዚህ ህፃናት፤ የጤና፣ የምግብ፣ የትምህርት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች የማግነት ነገር ፈተና ሆኖባቸዋል ተብሏል፡፡
‘’በህጉ መሰረት አንድ ህፃን ከወላጆቹ ጋር ማረሚያ መግባት የሚኖርበት እድሜው ከ2 ዓመት እስካለለፈው ድረስ ብቻ ቢሆንም ከዚያ በላይ የሆኑም እየገቡ እንደሆ’’ አቶ ኩምሳ ያስረዳሉ፡፡
ምንም እንኳ የተጠቀሱ ችግሮች ቢኖሩም ባለፉት 6 ዓመታት የተሻሻሉ አሰራሮችም እንዳሉ በጥናቱ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
ከእነዚህ መካከልም ‘’ከዓመታት በፊት በማረሚያ ቤቶች በተደጋጋሚ ፈጸማሉ ይልባሉ የነበሩ ማሰቃየቶች(ቶርቾ) አሁን ላይ ቀርተዋል ሲሉ ጥናት አቅራቢው ነግረውናል፡፡
ተደጋጋሚ ችግሮች ይታይባቸዋል ከተባሉ ማረሚያ በቶች መካከል በኦሮሚያ ክልል የሚገኙት ይገኙበታል፡፡
ሸገር ጉዳዩን በተመለከተ፤ የክልሉ ማረሚያ ቤት የኮሚሽነር ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንስፔክተር የማነ አቤቱን አነጋግሯል፡፡
ሀላፊው፤ የምግብ፣ የቤት ጥበት፣ ታራሚዎቹ የሚታከሙበት ቦታዎች ችግር መኖራቸውን አረጋግጠው፤ ‘’እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለመንግስት አቅርበን እየተሻሻሉ ነው’’ ብለውናል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል የኑስ ሙሉ፤ ‘’የተጠቀሱ ችግሮች ሁሉ እየተፈጠሩ ያሉት በቂ በጀት ስለሌለን ነው’’ ሲሉ ነግረውናል፡፡
‘’ወደፊት የችግቹን መጠን ለመቀነስ እየበረታን ነው፤ አቅም ያለው ሰውም ልክ መጽሐፍቶችን አምጥቶ እንደሚሠጥ ሁሉ በሌላውም ቢረዳን’’ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችን በአንድ ክፍል ከማቆየት ባለፈ በስነ ልቦናም ሆነ ሌሎች በሚታነፁባቸው ጉዳዮች ላይ በብርቱ ባለመሰራቱ አንዴ ከማረሚያ ቤት ገብተው የወጡ ሳይታረሙ ደጋግመው ወንጀል የሚፈጽሙ ብዙዎች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/bdfkxbad
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments