ነሐሴ 13፣2016 - የተለያዩ የገቢ እቃዎች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ ይውላል ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Aug 19, 2024
- 1 min read
የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ በላከው ደብዳቤ የተለያዩ ምርቶች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ ወይም በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር እንዲገቡ የተላለፈውን ውሳኔ ስራ ላይ እንዲያውል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

መንግስት የውጭ ምንዛሪ በገበያው እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ የገቢ ንግዱን ለማቀላጠፍ ያስችል ዘንድ ውሳኔው እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ከደብዳቤው እንደተመለከትነው እንዳይገቡ ከተከለከሉ ማለትም ከፀጥታ የደህንነት እቃዎች እንዲሁም ከነዳጅ አውቶሞቢሎች ውጭ ሌሎች ምርቶችን ያለ ውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ አገር ማስገባት ይቻላል ተብሏል፡፡
Comments