በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ ህጻናትን በተመለከተ ያሉ ዝርዝር ሀሳቦችን ወደ ታች አውርዶ ለመተግበር መመሪያ የሚያሻቸው ተለይተው እንዲሰራባቸው እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
ኢትዮጵያ ህጻናትን በተመለከተ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ህጎችን ተቀብላ እየተገበረች ቢሆንም ተግባራዊነቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም ማስፈጸሚያ መመሪያዎች ማሰናዳት ላይ መሰራት እንዳለበት ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ የቤተተሰብ ህግ በህጻናት የቀለብ አወሳሰን የተመለከተ ህግ ቢኖርም ውሳኔዎችን ለመስጠት የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ አልነበረውም ተብሏል፡፡
ለዚህም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስራውን ያቀላጥፋል የተባለ መመሪያ ተሰናድቷል፡፡
Comments