‘’ዛላንበሳ ጨምሮ በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ የኢሮብ አካባቢዎች ነዋሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው’’ ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ተናገረ፡፡
በዛላንበሳን ጨምሮ በኤርትራ ሰራዊት እጅ በሆኑ የኢሮብ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ ጽሕፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡
‘’የፌደራል መንግስት እና በሃወሃት መካከል ተደርጎ በነበረው ጦርነት ምክንያት በኤርትራ ሰራዊት እጅ የገቡ አካባቢዎች ባለመለቀቃቸው የአካባቢው ተወላጆች ላይ ችግር እየደረሳባቸው’’ እንዳለ የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ ፀሃዬ እንባዬ ነግረውናል፡፡
በኢሮብ የነበረው የባንክ፣ የስልክ እና መሰል አገልግሎት በጦርነቱ ወቅት ከተቋረጠ ወዲህ ዳግም አልተመለሰም ተብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ‘’በኤርትራ ሰራዊት እጅ ባሉ እና ከኢሮብ አካባቢ ወደ አዲግራት እንዲሁም ጎረቤት ከተሞች 100 ኪ.ሜ ለማይሞላ መንገድ 600 ብር እየከፈሉ’’ እንደሆነ ኃላፊው ነግረውናል፡፡
በተያዙ አካባቢዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ ናቸው መባሉን ሰምተናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments