ነሐሴ 13፣2016 - በህወሃት ምክትል ሊቀመንበርነት በሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር እና በሕወሃት ሊቀመንበር ደብረ ፂዮን መሀከል የተነሳው ልዩነት ወዴት ያመራ ይሆን?
- sheger1021fm
- Aug 19, 2024
- 1 min read
በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) ሊቀመንበርነት የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ከቀናት በፊት የጀመረውን 14ኛ ጉባኤውን ዛሬ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአሁኑ ወቅት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን በሚመሩት በህወሃት ምክትል ሊቀመንበር እና በፓርቲው ሊቀመንበር መከከል በተነሳው ልዩነት፤ የፓርቲውን ሊቀመንበር ጨምሮ 17 ነባር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እነ ዶ/ር ደብረፂዮን በጠሩት ጉባኤ ላይ አለመሳተፋቸው ተነግሯል፡፡
በዚህም ፓርቲው እንዳገዳቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡
ከትናንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩን የሚመሩትና የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ ምልልስ በዶ/ር ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቡድን የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስልጣን ለመንጠቅ ሙከራ ሊያደረግ ይችላል ብለው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
በህወሃት ምክትል ሊቀመንበርነት በሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር እና በሕወሃት ሊቀመንበር ደብረ ፂዮን መሀከል የተነሳው ልዩነት ወዴት ያመራ ይሆን?
የቀድሞ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት በአሁኑ ጊዜ የአረና ትግራይ ለሉአላዊነት ፓርቲ ሀላፊው አቶ ገብሩ አስራትን ሸገር ስለውዝግቡ ጠይቋል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
Kommentare