ባንኩ ይህን አገልግሎት ይዞ የመጣው ከማስተርካርድ ጋር በመተባበር እንደሆነ ተናግሯል፡፡
ዳሽን ባንክ ትናንት ምሽት በተከናወነ ሥነ- ሥርዓት ያስተዋወቀው የቨርቹዋል ዓለም አቀፍ ቅድመ ክፍያ ካርድ የተዘጋጀው ለዓለም አቀፍ ተጓዦች መሆኑ ተነግሯል፡፡
ይህ ካርድ ዳሽን ባንክ ከዚህ ቀደም ይዞ ከመጣቸው ካርዶች የሚለይበት ባህሪ እንዳለውም ሲነገር ሰምተናል፡፡
ካርዱን ወደ ገንዘብ መክፍያም ሆነ መቀበያ ማሽን ማስገባት ሳያስፈልግ ነክቶ ብቻ መክፈል ወይንም መቀበል የሚያስችል መሆኑ አንዱ የሚለየው ባህሪው መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስፋው አለሙ ተናግረዋል፡፡
ካርዱ አንድ ጊዜ ለደንበኞች ከተሰጠ በኋላ በካርዱ ላይ ያሉ ሚስጢር ቁጥሮችን ለመቀየር ወይንም ካርዱ ራሱ ቢጠፋ ወይንም ቢሰረቅ ደንበኛው በራሱ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችለው እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
በዳሸን ቅድመ ክፍያ ማስተርካርድ ደንበኞች ከኤቲኤም እና ፖስ በተጨማሪ በኢ-ኮሜርስ ክፍያ መክፈል የሚያስችላቸው ሲሆን ደንበኞች ፕላስቲክ ወይም ቨርቹዋል ካርድ በመውሰድ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል፡:
ከዚህ በተጨማሪ ፕላስቲክ ካርዱ ስም የታተመበትና ስም ያልታተመበት የካርድ አይነቶችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ደንበኞች ዳሸን ማስተር ካርድ ላይ የተሞላው የውጪ ምንዛሬ ሲያልቅ እንደገና በመሙላት መጠቀም የሚያስችላቸው ሲሆን ካርዱን ኤቲኤምና ፖስ ማሽን ላይ በማስገባት ወይም ያለ ንክኪ ገንዘብ ማውጣት ወይም ክፍያ መፈፀም ያስችላቸዋል፡፡
ይህ ዳሽን ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ይዞት የመጣው ቨርቩዋል ዓለም አቀፍ ቅድመ ክፍያ ካርድ ከፍተኛ የደህንነት መጠበቂያ የተሰራለት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡
ደንበኞች ካርዱን ለመጠቀም ወደ ዳሽን ባንክን ቅርንጫፍ በመሄድ ፓስፖርት፣ ቪዛ እና የበረራ ቲኬት በማሳየት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡
የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስፋው አለሙ በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ካርዱ ለደንበኞች ቀላል፣ ምቹና አስተማማኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የዳሽን ባንክ እና ማስተር ካርድ ከዚህ በተጨማሪ የንግድ ተቋማት ክፍያቸውን በበይነ መረብ ከየትኛውም የአለም ክፍል መቀበል የሚያስችል የማስተር ካርድ የክፍያ መቀበያ ጌትዌይ አስተዋውቋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios