መንኮራኩሯ ወደ ጨረቃ ምህዋር የገባችው ከመጠቀች ከ5 ቀናት ገደማ በኋላ እንደሆነ TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡
ሉና 25ን በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የማሳረፍ እቅድ መኖሩ ታውቋል፡፡
መንኮራኩሯ በዚያ ውሃ ይገኝ እንደሆነ የማጥናት ተልዕኮ አላት ተብሏል፡፡
ሉና 25 ለመጪዎቹ 10 አመታትም የተራዘመ ተልዕኮ እንደሚኖራት ተጠቅሷል፡፡
ሩሲያ ወደ ጨረቃዋ መኮራኩር ስታመጥቅ ከ47 አመታት በኋላ የሉና 25 የመጀመሪያው እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
![](https://static.wixstatic.com/media/b24dd6_0997e996a9214e6bb48e517f7055e6e5~mv2.jpg/v1/fill/w_900,h_600,al_c,q_85,enc_auto/b24dd6_0997e996a9214e6bb48e517f7055e6e5~mv2.jpg)
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
YouTube: t.ly/SHEGER
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments