top of page

ነሐሴ 10፣2016 - በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ላይ እስከ መገንጠል የሚለው አንቀጽ 39 እንዲሻሻል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጀንዳ አድርጎ ለምክክር ኮሚሽን አቀረበው

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ላይ እስከ መገንጠል የሚለው አንቀጽ 39 እንዲሻሻል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጀንዳ አድርጎ ለምክክር ኮሚሽን አቀረበው፡፡


ክልሉ ሐምሌ 23 ቀን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ አድርጎ ካቀረባቸው ጉዳዮች መካከል ውስጥ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 የራስን እድል በራሱ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል የሚለው በሚደረገው ሀገራዊ ምክክር አንዲሻሻል ጠይቋል፡፡


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ፋንታሁን መለሰ ህገ-መንግስቱ በሙሉ ሳይሆን አንቀጽ 39 ጨምሮ ሁሉን የማያስማሙ አንቀጾች እንዲሻሻሉ አጀንዳ አርገን ለኮሚሽኑ አቅርበናል ብለውናል፡፡


የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ እና የክልል አደረጃጀቶችን በተመለከተ ክልሉ ካቀረባቸው አጀንዳዎች መካከል ናቸው ተብሏል፡፡


አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ያለቸው የህብረተሰብ ከፍሎች በፖለቲካው ላይ ውክልና እንዲኖራቸው እና የፖለቲካ አመራሮች በስልጣን ላይ የሚኖራቸው ቆይታ ገደብ እንዲኖረው የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋትም እንዱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡


አንዱን የሚያጎላ ሌላውን የሚያሳንስ ሌላውን ዝቅ አድርጎ አንዱን ከፍ የሚደርጉ ትርክቶች እና ታሪኮቸም በምክክሩ እንዲታዩ አጀንዳ አድርገን ጠይቀናል ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራ ህብረት ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ፋንታሁን መለሰ ንግረውና፡፡


ባንዲራ ህገ-መንግስት፣ የክልል አደረጃጀት እና መሰል አጀንደዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጨማሪ አዲስ አበባም አጀንዳዎቼ ናቸው ማለቱን መዘገባቸው ይታወሳል፡፡





ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page