ነሀሴ 8 2017 - ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ወደ ግብጽም መሻገር አለበት ተባለ።
- sheger1021fm
- Aug 14
- 1 min read
ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ወደ ግብጽም መሻገር አለበት ተባለ።
ኢትዮጵያ ለተጨማሪ ሀገራት የኤሌክትሪክ ሀይልን ማቅረብ መቻሏ በቀጠናው የሚታየውን ውጥረት ማርገቢያ አንዱ አማራጭ መንገድ አድርጋ እንደምትወስደውም ተነግሯል።
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ለኬንያ እና ጅቡቲ በሽያጭ ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ118 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተነግሯል።
በዓመቱ ከመነጨው አጠቃላይ ሀይል ሰባት በመቶውን ለውጭ ገበያ ያቀረበችው ኢትዮጵያ አምስት በመቶውን ለኬንያ፣ ሁለት በመቶውን ለጅቡቲ ሸጣ ገቢውን ማግኘቷ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር) ሲናገሩ እንደሰማነው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ለጎረቤት ሀገራት በሽያጭ የምታቀርበው በአነስተኛ ዋጋ ነው። ይህም የራሱ የሆነ ምክንያት አለው ብለዋል።
ከኤሌክትሪክ ሽያጩ ከሚገኘው ገቢ በላይ የቀጠናው ሀገራት በሀይል መስመር መተሳሰራቸው አካባቢውን የበለጠ የሚያረጋጋ ነው ብለዋል።
የህዳሴው ግድብም የአፍሪካ ፕሮጀክት ነው እየተባለ የሚቀርበው በዙሪያ ያሉ ሀገራትም ሀይል በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት በመሆኑ ጭምር እንደሆነ ያስረዳሉ።
ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ያገናኘው መስመርም ከግብፅ ጋር ከዛም አልፎ በጆርዳን አውሮፓ መድረስ ይኖርበታል ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments