top of page

ነሀሴ 30 2017 የተበላሹ ወይም መጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶችን ሲሸጡ በተገኙ 85 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ።

  • sheger1021fm
  • Sep 5
  • 1 min read

ይህን ያለው የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ነው።

 

በተቋማቱ ላይ የተወሰደው እርምጃ ከሀምሌ ወር 2017 ዓ.ም ወዲህ በተደረገ የቁጥጥር ስራ መሆኑን ሰምተናል።

 

እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት ውስጥ 2 ሆቴሎች ላይም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ባለስልጣኑ ተናግሯል።

 

እርምጃ የተወሰደባቸው 5 ባለኮከብ ሆቴሎች መሆናቸውንም ሰምተናል።

 

ree

እርምጃ የተወሰደባቸው ሆቴሎች ከዚህ ቀደም የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ነው ተብሏል።

 

4 ተቋማት ደግሞ አገልግሎት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን ሌሎች ላይ ደግም አስተዳደራዊ እርምጃ ማለትም ምርቶች እንዲወገዱ እና እንዲታሸጉ ተደርጓል ተብሏል።

 

በሌላ በኩል ባለስልጣኑ በቅርቡ ለሚከበሩት ሀይማኖታዊና ሀገራዊ በዓላት እንዲሁም አለም አቀፍ ጉባኤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የቁጥጥር ስራውን እየከወነ መሆኑን ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።

 

በዚህም እንግዶች የሚያርፉባቸው እና አገልግሎት የሚያገኙባቸው ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና መዝናኛ ስፍራዎች ላይ የንፅህና እና የደህንነት ደረጃዎችን ለማረጋገጥ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ተብሏል።

 

መግለጫውን የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እመቤት ታደሰ ሆቴሎች የሚያቀርቧቸውን ምግብ እና መጠጦች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ቁጥጥር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

 

የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ሌሎች የጤና ተቋማት በትብብር ለጉባኤው ተሳታፊዎች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለማዘጋጀት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት መከናወናቸውንም ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

 

በዚህም 8 ሆስፒታሎች እና 5 የህክምና ማዕከሎች ተመርጠው የጤና አገልግሎት አሰጣጣቸውን በተመለከተ ዝርዝር የቁጥጥርና የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን ሰምተናል።

 

ባለስልጣኑ ከቁጥጥር ስራው ባሻገር አቅመ ደካሞችን በመርዳት እና ነፃ ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም ተናግሯል።

 

ፍቅሩ አምባቸው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page