ነሀሴ 27 2017 - በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተሰማርተው ሶፍትዌሮችን እያበለፀጉ ለተቋማት የሚያቀርቡ ድርጅቶች እየበረከቱ ነው
- sheger1021fm
- Sep 2
- 1 min read
በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተሰማርተው ሶፍትዌሮችን እያበለፀጉ ለተቋማት የሚያቀርቡ ድርጅቶች እየበረከቱ ነው፡፡
የድርጅቶቹ በዘርፉ መሰማራት የቴክኖሎጂው ዘርፍ ያለበትን እጥረት ያቃልላል ተብሏል፡፡
ወደእዚህ ዘርፍ እየመጡ ካሉ ተቋማት መካከል እንደሆነ የሚናገረው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ሶፍትዌሮችን እያበለፀገ ለባንኮች፣ ለአቪየሽን ዘርፍ ድርጅቶች እንዲሁም ለሌላውም እያቀረበ ይገኛል።

በሃገሪቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ክፍተት አለ ብለን ስለምናምን አሜሪካ ከሚገኘው ማሃሪሽ ኢንተርናሽናል ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂ የትምህርት ዓይነቶች ላይ ትኩረት አድርገን እያስተማርን ነው ብለውናል።
በዚህም ከትምህርቱ ጎን ለጎን በሚይዟቸው ፕሮጀክቶች ለመንግስት ተቋማት፣ ለባንኮችና በአቬሽኑ ዘርፍ ላሉ ድርጅቶች ሶፍትዌሮችን እንደሚያበለፅጉና ተማሪዎቻውም ከተመረቁ በኋላ ወደዚህ ስራ እንደሚቀላቀሉ የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አጥናፉ አስረድተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ኮሌጁ የኦላይን ትምህርቶችን የሚያስተምርበት STA አካዳሚ የተሰኘ ሶፍትዌር እንዳለው የሚናገሩት ፕሬዝዳንቱ ይህም እስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የኦላይን ስልጠና ወስደው ሰርተፊኬት ያገኙበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
የወቅቱ የትምህርት ዘርፍ ትልቁ ችግር ጥራት ነው፤ ኮሌጁ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ማስቻል ነው ያሉት ፕሬዝዳቱን በዚህ መንገድ አገኘነው ያሉትን ውጤትም ነግረውናል፡፡
ከ7 ዓመት በፊት ስራው ሲጀመር ዓላማችን አሜሪካ የሚገኘውን ማሃሪሽ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲን ኢትዮጵያ ውስጥ መክፈት ነበር ያሉት ዶ/ር አጥናፉ በራሱ ስም እዚህ ዩኒቨርሲቲ መክፈት ስለማይቻልና በአሜሪካ ያለውን የትምህርት ጥራት እዚህ ማምጣት ስለምንፈልግ ስሙን ተውሰን አሜሪካ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ብለነዋል ሲሉም አስረድተዋል።
ኮሌጁ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሊደር ሺፕና በፕሮጀክት ማኔጅመንት በቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 350 ተማሪዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ አስመርቋል።
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments