ነሀሴ 1 2017 - በት/ት ዘርፍ ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ያመጡት አሉታዊና አዎንታዊ ለውጥ በጥናት መፈተሽ አለበት ተባለ
- sheger1021fm
- Aug 7
- 1 min read
በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ያመጡት አሉታዊና አዎንታዊ ለውጥ በጥናት መፈተሽ አለበት ተባለ፡፡
ይህን ያሉን ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሞያ ናቸው፡፡
ባለፉት ተከታታይ 3 ዓመታት የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ዝቅ ማለቱን ተከትሎ በ #ተማሪዎች የመማር ፍላጎት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያመጣ ስጋት አለን የሚሉ ባለሞያዎች በተለያዩ ጊዜያት እየተደመጡ ነው፡፡
እነዚህ ባለሞያዎች እንደሚሉት አብዛኛው ተማሪ ውጤት እየመጣለት ባለመሆኑ በትምህርት ዘርፍ ላይ ተስፋ እንዳይቆርጥ ስጋት አለን በማለት ሲናገሩ ይሰማል፡፡
የትምህርት ባለሞያና በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዳምጠው ወልዴ(ዶ/ር) አሁን ያለው ተማሪ ከፈተና ውጤት ጀምሮ በየጊዜው የሚያያቸው ቴክኖሎጂዎች በትምህርት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ እያደረገው ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ጥናት አልተደረገም ችግሩ ከስር መሰረቱ በሚገባ ለማወቅና ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ለመስጠት ጥናትና ምርምር ሊደረግ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተማሪዎች ፈተናዎችን በራስ አቅም ከመስራት ይልቅ እንደቻት ጂፒቲ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለመስራት ይሞክራሉ በማለት ጠቅሰዋል፡፡
ተማሪዎች የሚወስዱት ፈተና በትክክል የተማሩትን ትምህርት ይመዝናል ወይ? ምን ያህል እንዳወቁ ለመገንዘብ የሚያስችል ጥያቄ ነው የሚወጣው በሚለው ዙሪያ በሳይንሳዊ መንገድ መፈተሽ አለበት ይላሉ ዶክተር ዳምጠው፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ከኩረጃ እንዲፀዳ ለማድረግ የወሰደው እርምጃ የሚበረታታ ነው ነገር ግን ኩረጃን ለማስቀረት የወሰዳቸው እርምጃዎች በተለይም ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲ መፈተን ምን ያክል ውጤታማ ነው? በተማሪዎች ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ይበልጡኑ በስነልቦና የሚለው በጥናት ሊታወቅ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyu.com/ycxjmm3s












Comments