ገዳ ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ ጋር በመሆን የፈጣን ምላሽ ኮድ(ኪው አር ኮድ) የተሰኘውን አገልግሎት ጀምሬአለሁ አለ፡፡
ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ ዲጂታል እና የዘመናዊ ግብይት ተጠቃሚ የሆነ ማህበረሰብን ለማብዛት እንዲሁም የክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን ያግዛል የተባለለት የፈጣን ምላሽ ኮድ ወይም ኪው አር ኮድ የተሰኘው የክፍያ ሥርዓት ወደ አገልግሎት መግባቱን ባንኩ እወቁልኝ ብሏል፡፡

ወደ ስራ የገባው ይሄው የክፍያ ሥርዓት ለሆቴሎች፣ ለካፌዎች፣ ለሱቆች እና ለሌሎች የቢዝነስ ተቋማት የሚያገለግል መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ከሱ በተጨማሪም በኦንላይን ለሚሰሩ ነጋዴዎችም ሆነ ተጠቃሚዎችም የሚያገለግል ነው ይላሉ፡፡
በገዳ ባንክ እና በሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ ይፋ የሆነው የፈጣን ምላሽ ኮድ ወይንም ኪው አር ኮድ አገልግሎት ነጋዴው እና ባንኩን የሚያግዝ ነው ተብሎለታል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት አመት ባንኩ ጠቅላላ ሀብቴ ወደ 5.3 ቢሊየን ብር አድጓል ያለ ሲሆን ከደንበኞቼ የሰበሰብኩት ገንዘብ ደግሞ ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ነው ብሏል፡፡
ገዳ ባንክ ወደ ስራ ከገባ 18 ወራት ተቆጥረዋል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Commentaires