top of page

ነሀሴ 1፣2016 - ከሰሞኑ ባንዳንድ የመንግስት የህክምና ተቋማት የመድኃኒት መደብሮች ላይ ለስኳር ህመም የሚሆን መድኃኒት እጥረት መኖሩን ተከትሎ ያቅርቦቱ ጉዳይ እንዴት ነው?

  • sheger1021fm
  • Aug 7, 2024
  • 1 min read

በጤና ተቋማት ላይ የሚከሰት የመድሀኒት እጥረትን ተከትሎ ጥያቄው ዘወትር ወደ እኔ ቢመጣም የህክምና ተቋማት ያለባቸውን ውዝፍ የመድሀኒት እዳ በጊዜ ያለመክፈላቸው እና ፍላጎታቸውን አለማሳወቃቸው ለችግሩ ዋና ምክንያት ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ተናገረ።


ከሰሞኑ ባንዳንድ የመንግስት #የህክምና_ተቋማት የመድኃኒት መደብሮች ላይ ለስኳር ህመም የሚሆን መድኃኒት እጥረት መኖሩን ተከትሎ ያቅርቦቱ ጉዳይ እንዴት ነው? ስንል መድኃኒት አቅራቢውን ተቋም ጠይቀናል።


በመድሃኒት ግዥ በኩል በተለይ የስኳር #መድሀኒት በበቂ ሁኔታ ግዥ ተፈጽሟል ያሉን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አወል ሀሰን ለመጪዎቹ 8 ወራት ድረስ የሚሆን ክምት እንዳለ ነግረውናል።


በመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓት ውስጥ ብዙ ባለድርሻዎች አሉ የሚሉት አቶ አወል ነገር ግን የመድኃኒት እጥረት በተቋማት ላይ ሲከሰት ቅድሚያ የሚጠይቀው ይኸው ተቋም ቢሆንም የህክምና ተቋማት በዱቤ የወሰዱትን መድሃኒት ክፍያ በጊዜ ያለመፈፀም እና ፍላጎታቸውን ማሳወቅ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ለሚፈጠረው ጥረት ምክንያት ነው ብለዋል።


ከዱቤ አገልግሎቱ ጋር በተያያዘም ውዝፍ ያለባቸውን በመለየት ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ተብሏል።


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በአጠቃላይ አንድ ሺህ ሃያ የተለያዩ ዓይነት የህክምና ግባቶችና መድሃኒቶችን በተለያዩ ፕሮግራሞች ለሆስፒታሎችና ህክምና ተቋማት እንደሚያቀርብ ሰምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ.. https://tinyurl.com/3nubux9c


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page